የሰበካ መንፈሳዊ ጉቤኤው የአስመራጭ ኮሚቴ መልእክት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

+በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
ለሐመረ ብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤተክርስትያን አባላት፡
በእግዚአብሔር ስም ሰላምታችንን እያቀረብን የፊታችን እሑድ ነሐሴ 23 2013 (08/29/21) ልናደርገው የነበረውን የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ምርጫ በቂ አባላት ባለመምረጣቸውና የተመረጡት እጩዎች ቁጥርም ከተጠበቀው በታች ስለሆነ፤ የአስመራጭ ኮሚቴው ካለው ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ጋር ተነጋግሮ ምርጫውን ላልተወሰነ ጊዜ አራዝሟል። የሚቀጥለውንም የምርጫ ሂደት ሰበካ ጉባኤው ወደፊት የሚያውቀን ይሆናል። ለተሳተፋችሁ አባላት ምስጋናችንን እያቀረብን፣ ያልተሳተፋችሁም ለወደፊቱ በመሳተፍ ለቤተክርስቲያናችን ግዴታችሁን እንድትወጡ በትህትና እናሳስባለን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለ መስቀሉ ክቡር አሜን!+

የአስመራጭ ኮሚቴ

Phone – 301 – 910-2005
 ወ/ሮ ሀና አስፋው
የአስመራጭ ኮሚቴ ሕዝብ ግኑኝነት፣
እግዚአብሔር አንድነታችንን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

ነሐሴ 21 ቀን 2013ዓም/Aug 27, 2021