የሰበካ መንፈሳዊ ጉቤኤው የአስመራጭ ኮሚቴ መልእክት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ለሐመረ ብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ አባላት በሙሉ እንደሚታወቀው እሑድ ነሐሴ 02/2013 (Aug 8/2021 ) እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ በአባቶች ጸሎት በጸሎተ ዕጣን ከ 11AM – 5 PM ለቤተክርስቲያናችን ይጠቅሙናል ያገለገሉናል የምትሏቸውን የምትመርጡበት ቀን ነው። ከላይ የመለያ ቁጥር ያለው የምርጫ ካርድ ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኅል። በዚህም መሰረት ከካህናት ሁለት ፣ ከሰንበት ት/ቤት አንድ፣ ከምእመናን አምስት፣ በመምረጥ የነቃ ተሳትፎ ታደርጉ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን ::


ሌላው :- ምርጫ ኮሚቴ “ምን አልባት የምርጫው ቀን እሑድ ነሐሴ 02/2013 (Aug 8/2021) መገኘት ባትችሉ ብሎ በማሰብ” የቅድመ ምርጫ (Absentee vote) አዘጋጅቷል። Aug 05, Aug 06, and Aug 07 ከ5:00 PM እስከ 9:00 PM ድረስ መጥታችሁ የምትመርጡበትን ጊዜ አመቻችቶ ይጠበቃችኅልና መጥታችሁ ትመርጡ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን ።
የልዑል እግዚአብሔር ቸርነት የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነን የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ምልጃ የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃ አይለየን አሜን


የምርጫ ኮሚቴ
 
Phone – 301 – 910-2005
 ወ/ሮ ሀና አስፋው
 የምርጫ ኮሚቴ ሕዝብ ግኑኝነት፣
እግዚአብሔር አንድነታችንን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

ሐምሌ 25 ቀን 2013ዓም/Aug 1, 2021