ለአባላት

የሐመረ ብርሃን ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤተ ክርስቲያን በዲሲ እና አካባቢው ሃገረ ስብከት ውስጥ ሆኖ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓትና ቀኖና መሰረት የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለምእመናን በሙሉ የሚሰጥ ሲሆን ለዚህ አገልግሎት መሰጠት ትልቁን ድርሻ የሚወስዱት በአጥቢያው ሰበካ ጉባኤ ተመዝግበው ያሉ አባላት ናቸው። ይህ ገጽ ለቤተ ክርስቲያኑ አባላቶች ያገለግላሉ ወይም ይጠቅማሉ የምንላቸውን መረጃዎች የምናስተላልፍበት ነው።

የክፍያ መረጃ (Aplos)

የአባልነት እንዲሁም ሌሎች ክፍያዎችን የፈጸሙበትን መረጃ ለማግኘት ይህን ማስፈንጠሪያ (link) በመጫን ማግኘት ይችላሉ። አፕሎስ (Aplos) ድረ ገጽ ላይ ከዚህ በፊት ተመዝግበው ካልነበረ መመዝገብ ይኖርቦታል (create an account)። እንዴት መመዝገብ እዳለቦት እና የሂሳብ መረጃውን እንዴት እንደሚያገኙ ዝርዝር መረጃ የያዘ ገጽ ነው። የበለጠ ጥያቄ ካለዎት ለቤ/ክኑ ሂሳብ ክፍል በ[email protected] ጥያቄዎትን መላክ ይችላሉ።

መተዳደርያ ደንብ (bylaws)

ቤተክርስቲያናችን ከምሥረታው ጀመሮ የምትጠቀምበት የመተዳደርያ ደንብ ሊንኩን በመጫን ማግኘት ይችላሉ።


እግዚአብሔር ይስጥልን። የመጥምቁ ዮሐንስ አማላጅነት የልዑል እግዚአብሔር ቸርነት አይለየን።